top of page

የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ3 ዓመት በፊት ቃል የገቡትን የውኃ ችግር እንዲፈቱላቸው ጠየቁ


Photo: Reporter Ethiopia

SOURCE: REPORTER ETHIOPIA

የኤሌክትሪክ ኃይልን ጨምሮ ከአማራ ክልል ጋር ስለተፈጠሩ ግጭቶች ጥያቄ አቅርበዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሐምሌ 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ከመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ከሦስት ዓመታት በፊት ቃል የገቡላቸውን የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ችግር እንዲፈቱላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡ ከውኃ በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል ችግራቸውም በፌደራል መንግሥት እልባት እንዲያገኝ ጠይቀዋል፡፡

የመቐለ ከተማ አዛውንቶች፣ ነጋዴዎችና ወጣቶች እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞችን የወከሉ ግለሰቦች ጥያቄያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበዋል፡፡ የከተማዋ ነዋሪዎች ዋና ዋና ችግሮች የመጠጥ ውኃና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግሮች መሆናቸውን ደጋግመው ገልጸዋል፡፡ የትግራይ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አሰፋ ገብረ ሥላሴ፣ ሕዝቡ በወር አንዴ ወይም ሁለቴ ውኃ ማግኘቱ ተስፋ አስቆርጦት እንደቆየ ተናግረዋል፡፡

ሆኖም የመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት ለከተማዋ ነዋሪዎች መፍትሔ ይዞ በመምጣቱ፣ የተስፋ ጭላንጭል እንዲታያቸው ማድረጉንም ጠቁመዋል፡፡ በኤሌክትሪክ ኃይል ረገድም ክልሉ ከፍተኛ ችግሮች ስላሉ፣ የኃይል አቅርቦትም እንዲፋጠን ጠይቀዋል፡፡ ‹‹ክልላችን በጦርነትና በድርቅ የተራቆተ እንደመሆኑ፣ ትልልቅ ግድብና መስኖ ያስፈልገናል፡፡ የፌደራል መንግሥት ትልቅ የግድብ ግንባታ እንዲካሄድ ትኩረት ይስጥበት፤›› ብለዋል፡፡

እናቶችም ልጆቻቸውን ለትግል በመሰዋት ለውጥ እንዲመጣ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ጠቅሰው፣ ‹‹የትግራይ እናት ሰላም ለማግኘት ልጆቿን ገብራ ትግሉን ለዚህ ለውጥ ብታበቃም በውኃ እጦት እየተጠማች ነው፤›› ያሉ አንዲት እናት የክልሉ ብቻ ሳይሆኑ ለአገሪቱ ሰላም የታገሉ እናቶች ለምን እንዲህ ያለው ችግር እንደሚጠናባቸው ጠይቀዋል፡፡

አቶ አሰፋም ሆኑ ሌሎችም የከተማዋ ነዋሪዎች አንዳንዶች የልዩነት ችግር እንዳለ በማስመሰል ተፋቅሮ የሚኖረውን ሕዝብ፣ ትግራይ የልዩ ተጠቃሚ ክልል እንደሆነች በማስመሰል በሚነዙት ወሬ ችግር እየተፈጠረ በመሆኑ የፌደራል መንግሥት ምን እየሠራ እንደሚገኝ ጠይቀዋል፡፡

READ በአዲስ አበባ ከተማ የሚፈናቀል ነዋሪ የለም ተባለ

ከእነዚህ ጥያቄዎች በተጨማሪ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ምክንያት ሰላምም ጦርነትም የሌለበት ቀጣና ውስጥ ስለሚገኙ አካባቢዎች ጉዳይ፣ ስለክልሉ ወጣት ሥራ አጦች፣ ፋብሪካዎች ለሠራተኞች ስለሚከፍሉት አነስተኛ ደመወዝ ጉዳይ፣ ስለሳዑዲ ተመላሾች፣ ቱሪስቶች በመንገድ ችግር ምክንያት ሊጎበኟቸው ስላልቻሉ የክልሉ ቅርሶች፣ ስለመንግሥት አመራሮች የትምህርት ዕድልና ስለሌሎችም ጉዳዮች ያነሷቸውን ጥያቄዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበዋል፡፡

 

Copyrights Disclaimer: BOLEPOST.COM is a video and news aggregator; thus, we claim no ownership of copyrighted videos and audios posted here on our website or shared via our social media pages. Videos, audios, images and other published materials on our website and social media pages must be treated as such.

bottom of page