
(ETV) : የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢሶህዴፓ/ አቶ አህመድ ሽዴን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ።
የኢሶህዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት ሶስት ቀናት በክልሉ ተፈጥሮ በነበረው ሁኔታ ላይ ጥልቅ ግምገማ ካደረገ በኋላ የድርጅቱ ሊቀመንበር የነበሩትን አቶ አብዲ መሃሙድን በአቶ አህመድን ሽዴ ተክቷል።
ኢሶህዴፓ በክልሉ የተከሰተውን ችግር ለማረም ለማስተካከልና አጠቃላይ በክልሉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ጠንክሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ለኢቲቪ በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡
#KanatvKanadramaEBSTVJtvethiopiaNewEth #ahmedshide #abdiilley #somali #somlia #jigjiga #abiyuahmed #shashamane