top of page

የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ወቅታዊ ጉዳዮችን በሚመለከት የሚወሰዱ እርምጃዎች ላይ እየተወያየ ነው


Photo:Daniel Getachew /Reporter Ethiopia

Reporter Ethiopia (Nov. 10, 2017) : በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ በብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ የሚመራው የብሔራዊ ደኅንነትና የክልል ደኅንነት አባላት የሚሳተፉበት ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እየተካሄደ ነው፡፡

በስብሰባው ላይ በወቅታዊ ሁኔታዎችና በቀጣይ መወሰድ ባለባቸው እርምጃዎች ላይ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ሲሆን፣ ዛሬ ኅዳር 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ ውሳኔዎቹ ይታወቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በውይይቱ ላይ የክልል ርዕሳነ መስተዳድርና የደኅንነት ኃላፊዎች እየተሳተፉ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡

(C) Reporter Ethiopia

#HailemariamDesalegn #reporterethiopia #Reporter #Ethiopianews #TPLFnews #EPRDFNews #AddisAbaba #habeshanews #AmharicNews #Oromia #EastAfrica

bottom of page